Recent News

ኢንተርፕራይዙ ተኪ ምርቶች ማምረት ላይ አበረታች ውጤት ማሳየቱን ቦርዱ ገለጸ።

የኢንስቲትዩቱ ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ልማት ኢንተርፕራዝ የሥራ አመራር ቦርድ የኢንተርፕራይዙን የስራ እንቅስቃሴ በመገምገም ውሳኔዎችን አስተላልፏል። በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ሰብሳቢነት ሦስት አጀንዳዎች ላይ የተወያየው ቦርዱ የአፈጻጸም ውሳኔም አስተላልፏል።   ዶ/ር ብሩክ ኢንተርፕራይዙ የቦርዱን ውሳኔዎች በትኩረት ለቅሞ እየፈጸመ መሆኑ የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ተኪ ምርቶችን ለማምረት እየሠራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን የገለጹት ሰብሳቢው ተጠናረው እንዲቀጥሉ ራሱን እያስተዋወቀ መቀጠል እና ፕሮጀክቶችን ማፈላለግ እንደሚገባ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ሲቋቋም ከያዛቸው ግቦች መካከል ስልጠናን ከምርት ጋር ለማስተሳሰር የተሄደበት ርቀት በጥንካሬ የታዩ እንደሆኑ ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ ኢንተርፕራይዙ ከልምምድ ወጥቶ ተወዳዳሪ እየሆነ የመጣ ኢንተርፕራይዝ መሆኑን ገልጸው አሁንም ይበልጥ ተጠናክሮ ለመውጣት ማቀድ ይገባል ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት እና በጥራት መፈጸም ላይ ይበልጥ ትኩረት ተደርጎ ሊሰራ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡   ይህ ዓመት የኢንስቲትዩቱ የስትራቴጂክ ዓመቱ ማብቂያ በመሆኑ የኢንተርፕራይዙ ስኬት ለኢንስቲትዩቱ ስትራቴጂክ ዓመቱን ስኬት አንዱ ተጨማሪ ፋይዳ እንደሚኖረው ም/ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡   የኢንተርፕራይዙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ለሚ ቱጆ ያለፋትን ወራት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ቦርዱ በኢንተርፕራይዙ ስራ አፈጻጸም መቀጠል ስላሉባቸውና መሻሻል ስለሚገቡ ነገሮች ዝርዝር ውይይት ተደርጓል። ቦርዱ በሁለተኛ አጀንዳነት በውጭ ኦዲት የተሰራውን ሪፖርት አዳምጦ አጽድቋል። በሦስተኛነት ኢንተርፕራዙ ኢንስቲትዩቱን መደጎም በሚያስችለው አማራጭ ላይ በቀረበው ሰነድ ቦርዱ የተወያየ ሲሆን ገንቢ ሀሳቦችን በማከል በአገሪቱ የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትን ለማስተዳደር በወጣው ህግ መሰረት ተግባራዊ እንዲደረግ በውሳኔው አጽቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ዶ/ር ብሩክ ከድር በመጨረሻም ኢንተርፕራይዙ ተኪ ምርት ላይ በቀጣይም ይበልጥ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ፣ የገበያ ትስስር እንዲፈጥር፣ የ21ኛው ክ/ዘመን ት/ቤትን የማስተዳደር ሥራው በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

23/05/2026
በሞተር ሳይክል ጥገና እና ማሽከርከር የሰለጠኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተመረቁ።

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ቴክኖቢዚያ የኢንደስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ በሞተር ሳይክል ጥገና እና ማሽከርከር ያሰለጠናቸውን የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አስመርቋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በሠልጣኞቹ ምረቃ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መሠል ስልጠናዎች የመከላከያ ተቋምን ለማዘመን አስቻይ ናቸው ብለዋል። መከላከያ ሠራዊታችን ከጊዜ ወደጊዜ ራሱን እያዘመነ ነው ያሉት ዶ/ር ብሩክ በየጊዜው ከሚሠራቸው ፈጠራ የታከለባቸው ሥራዎች መካከል መሰል የሰውሀይል ልማት ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል። በመከላከያ የተጀመሩ ለውጦችን መደገፍ የሁሉም ተቋም ድርሻ እንደሆነ ገልጸው ኢንስቲትዩቱ እነዚህን ብቁ ባለሙያዎች በማፍራቱ የድርሻውን እያበረከተ መሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል። ኢንተርፕራይዝ መመስረት ያስፈለገው ፈጠራን ለማበረታታት መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ ቴክኖቢዚያ የኢንደስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ ይህንን ስልጠና በብቃት አዘጋጅቶ ለምረቃ በመብቃቱ ሊበረታታ ይገባል ብለዋል። ትብብሩ በዘርፈብዙ ጉዳዮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጨምረው ገልጸዋል። በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻ እዝ ምክትል አዛዥ ሜጄር ጀነራል ከማል ኤቢሶ በበኩላቸው፣ የሞተርሳይክል ጥገናና ሾፌር ስልጠና በአይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ መሆኑን ገልጸው ኢንስቲትዩቱ ይህንን ስልጠና ሰጥቶ ብቁ ሙያተኞችን ሥላፈራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህ ስልጠና ኢንስቲትዩቱ ያለውን የማሰልጠን እና የፈጠራ አቅም በሚገባ እንድንረዳ አስችሏል ብለዋል። የቴክኖቢዚያ ኢንደስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ ሥራ አስኪያጅ የስልጠናውን ቆይታ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሥነስርዓቱ ላይ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሚንስትር አማካሪ፣ ወ/ሮ ትዕግስት አሰፋ የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተወካይ፣ ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።

10/05/2026
ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ ለሠራተኞች የትንሳኤ በአል መዋያ ስጦታ አበረከተ።

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ "እያመረተ ለማሰልጠን" የተቋቋመ ኢንተርፕራይዝ ነው። ኢንተርፕራይዙ የትንሳኤ በአልን ምክንያት በማድረግ 1.5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የበአል መዋያ ስጦታ ለ194 ሰራተኞች አበርክቷል። ይህም ኢንተርፕራይዙ ከቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ስራዎች በተጨማሪ በማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ እየተሠማራ እንደሆነ ማሳያ ነው ሲሉ የኢንተርፕራይዙ ሥራ አስኪያጅ አቶ ለሚ ቱጆ ገልጸዋል። ቴክኖቢዚያ የኢንደስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ የኢንስቲትዩቱ ተልዕኮዎች የሆኑትን ስልጠናን፣ ጥናትና ምርምርን እና የቴክኖሎጂ ፈጠራን ለማስተሳሰር እየሰራ ይገኛል። በአሁኑ ሰአት በአገራችን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲመረቱ፣ በስፋትም ወደ ተጠቃሚዎች እንዲደርሱ በስፋት እየሰራ ያለ ተቋም ሆኗል።

24/04/2025
ቦርዱ የቴክኖቢዚያ የኢንደስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ የ6 ወራት አፈጻጸምን ገመገመ፡፡

በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ቴክኖቢዚያ የኢንደስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ የበጀት ዓመቱን የ6 ወራት ዕቅድ ፈጻጸም ለቦርዱ አቅርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ኢንተርፕራይዙ የያዛቸው ፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ የመደበኛ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም የውይይት አጀንዳ ሲሆኑ የኦዲት ሪፖርትም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ እና የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ከተመሰረተ አንድ ዓመት የሞላው ኢንተርፕራይዙ ከምስረታ እና የዝግጅት ጊዜ አልፎ በርካታ ተግባራትን መፈጸም መቻሉን ገልጸዋል፡፡ ኢንተርፕራዙ ለመሰል ተቋማት ሞዴል ተቋም እንዲሆን ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል። የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ በበኩላቸው ኢንተርፕራይዙ ሲቋቋም የተለመዱ ስራዎችን ለመስራት ሳይሆን በዘርፉ አዲስ ባህል ለመፍጠር ነው ብለዋል። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ ከውጪ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን ማምረት መቻሉ ትልቅ እመርታ ነው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሯ በተለያዩ መለኪያ መስፈርቶች ተወዳዳሪነቱን ማጠናከር አለበት ብለዋል። የኢንተርፕራይዙ ስራአስኪያጅ አቶ ለሚ ቱጆ ባለፉት ስድስት ወራት የተፈጸሙ ተግባራት ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በአገልግሎት ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎችን አቅርበል፡፡ እንደአገር የመጀመሪያ የሆነ የተሸከርካሪ ጎማ መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ፋብሪካ በራስ አቅም ተሰርቶ ወደስራ መግባቱን በትልቁ የጠቀሱት አፈጻጸም ነው፡፡ ቴክሎጂዎችን በስፋት የማምረት ስራ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች ላይ ለመስራት የቴክኖሎጂ ልየታ መካሄዱን ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ረጃጅም ወንዞችን የሚሻገሩ ተንጠልጣይ ድልድዮችን ሰርተው ለተጠቃሚው ማድረስ መቻሉንም ስራአስኪጁ በሪፖርታቸው ገልጸዋል። በሥራናክህሎት ሚኒስቴር በኩል ለዓለምአቀፍ የስራ ገበያ ብቁ የሆኑ ሾፌሮችን የማሰልጠን ስራ እየተሰራ መሆኑም ሌላው ኢንተርፕራይዙ በስኬት ከፈጸማቸው ተግባራት መካከል ተጠቅሷል፡፡ "እያመረትን እናሰለጥናለን" በሚል መርህ የተቋቋመው ኢንተርፕራይዙ ይህንኑ ተልዕኮ ለማሳካት ከኢንስቲትዩቱ ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑ ገልጸው ይበልጥ ትስስሩን ለማጠናከር የአሰራር ማንዋል የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይ ለቦርድ ይቀርባል ብለዋል። በጋርመንት እና ሌዘር ዘርፎ የተማሪዎች ዩኒፎርም ማምረት፣ ቦርሳ ማምረት እንዲሁ ከበርካታ የፕሮጀክት አፈጻጸሞቹ መካከል የተነሳ ነው፡፡ የቦርድ አባላትም ኢንተርፕራይዙ በአጭር ጊዜ ትልቅ ትምህርት ሊወሰድበት የሚችል አፈጻጸም መፈጸም መቻሉን አድንቀው ይበልጥ ሊጠናከር ይገባል ያሏቸውን ሐሳቦች አንስተዋል። በመጨረሻም የቦርዱ ሰብሳቢ ዶ/ር ብሩክ ከድር እስከ ቀጣዩ የቦርድ የግንኙነት ጊዜ ሊሰሩ ይገባል ያሏቸውን አቅጣጫዎች አስቀምጠው ውይይቱ ተጠናቅቋል።

10/02/2025
ኢንስቲትዩቱ በመጀመሪያ ዙር በአሽከርካሪነት ሙያ ያሰለጠናቸውን ዜጎች አስመረቀ፡፡

በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ‹‹ኢትዮ-ቻይና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ት/ቤት›› ለውጪ አገራት ስራ ስምሪት የሰለጠኑ አሽከርካሪዎች ተመዝነው ብቁ መሆናቸው በመረጋገጡ ከኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር እጅ ምስክር ወረቀታቸውን ተቀብለዋል፡፡ ‹‹ዜጎች ብቁ እና በሥነ-ምግባራቸው የታነጹ ቢሆኑ ራሳቸውን ጠቅመው አገራቸውንም በበጎ ያስጠራሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከክህሎት ስልጠና በተጨማሪ በየመዳረሻዎቻቸው ‹‹ሙያዊ አምባሳደርነት›› እንዲወጡ የሚያስችላቸው ስልጠና እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተለያዩ አገራት ጋር እየፈጠረ ባለው ትስስር በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑና በከፊል የሰለጠኑ ሙያተኞችን ለመላክ በያዘው መርሃግብር አንዱ የአሸከርካሪነት ሙያ አንዱ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎቢዚያ ኢንተርራይዝ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም በአዲስ አዋቅሮ ቁሰቁሶችን አሟቶ ስልጠና በመስጠት ብቁ ዜጎችን እያፈራ ይገኛል ብለዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ‹‹ኢትዮ-ቻይና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ት/ቤት›› ሃላፊ አቶ ቴዎድሮስ የኋላሸት ለመጀመሪ ዙር ስልጠና ከበርካታ አመልካቾችና ተፈታኞች መካከል 140 ሰለጣኞችን ብቁ የሚያደርግ ቴክኒካዊና ባህርያዊ ስልጠና መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡ በሥነባህርይ፣ የመንገድ ደህንነት፣ አዲስ ቴክኖሎጂ መላመድን፣ እና ዘመናዊ ተሸከርካሪዎችን መጠገን ላይ ሰልጥነዋል ብለዋል፡፡ ስልጠናው ቀጣይነት እንደሚኖረው አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል፡፡

01/11/2024
Garment Section Delivers Workwear Materials for Educational Materials Production Enterprise

We are pleased to announce that the Garment Section of Technobizia has successfully completed the production and delivery of high-quality workwear materials for the Educational Materials Production Enterprise (EMPE). This delivery marks a significant step in our ongoing partnership with EMPE to support their workforce with durable, functional, and comfortable work attire.

21/10/2024
Announcement: Completed Greenery, Landscape Development, and Refurbishing Project at CCE

We are pleased to announce the successful completion of the Greenery, Landscape Development, and Refurbishing Project at the CCE (Civil and Construction Engineering) complex. This project represents our commitment to creating environmentally sustainable, aesthetically pleasing spaces that enhance both the functionality and beauty of the CCE campus.

21/10/2024
Steel Suspension Bridge Fabrication on going at CEE workshop.

We are excited to share that Steel Suspension Bridge Fabrication is currently underway at the CEE (Civil and Environmental Engineering) Workshop. This project represents a significant step forward in our efforts to innovate and contribute to large-scale infrastructure development.

21/10/2024
Ethio-China Drivers Training School Begins Registration for New Students

The Ethio-China Drivers Training School is pleased to announce the start of registration for new students. Aspiring drivers are invited to enroll in our comprehensive training programs, which are designed to provide the highest quality instruction and ensure that all students are fully prepared to obtain their driving licenses. the driving license categories can be generally described as follows: ሞተርሳይክል (Motorcycle) አውቶሞቲቭ (Automotive), ህዝብ 1 (Public 1), ህዝብ 2 (Public 2), ህዝብ 3 (Public 3), ደረቅ 1 (Dry Cargo 1), ደረቅ 2 (Dry Cargo 2), ደረቅ 3 (Dry Cargo 3), ፈሳሽ (Liquid Cargo),

18/08/2024
FDRE Technical and Vocational Training Institute Technobizia participated in a coffee plantation in Jimma Seka Cheqorsa with the local community.

FDRE technical and vocational training institute Technobizia has started working with the motto "We train while producing!!" So Ethiopia has been deployed in different fields of work to be the owner of its own products and one of them is agriculture that is focused on. Technobizia is working to make Ethiopia have a better tea production and they participated in a tea plantation in Jimma Soka Chekorsa with the local community.

14/08/2024

የኢንስቲትዩቱ ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ልማት ኢንተርፕራዝ የሥራ አመራር ቦርድ የኢንተርፕራይዙን የስራ እንቅስቃሴ በመገምገም ውሳኔዎችን አስተላልፏል። በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት...

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ቴክኖቢዚያ የኢንደስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ በሞተር ሳይክል ጥገና እና ማሽከርከር ያሰለጠናቸውን የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አስመርቋል። የኢንስቲትዩቱ...

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ "እያመረተ ለማሰልጠን" የተቋቋመ ኢንተርፕራይዝ ነው። ኢንተርፕራይዙ የትንሳኤ በአልን ምክንያት በማድረግ 1.5...

በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ቴክኖቢዚያ የኢንደስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ የበጀት ዓመቱን የ6 ወራት ዕቅድ ፈጻጸም ለቦርዱ አቅርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ኢንተርፕራይዙ...

Our enterprise has signed an agreement for the establishment of Training and Entrepreneurship Development Excellence Center as part to Consultancy...

በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ‹‹ኢትዮ-ቻይና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ት/ቤት›› ለውጪ አገራት ስራ ስምሪት የሰለጠኑ አሽከርካሪዎች ተመዝነው ብቁ መሆናቸው በመረጋገጡ ከኢንስቲትዩቱ...

We are pleased to announce that the Garment Section of Technobizia has successfully completed the production and delivery of high-quality...

We are pleased to announce the successful completion of the Greenery, Landscape Development, and Refurbishing Project at the CCE (Civil...

We are excited to share that Steel Suspension Bridge Fabrication is currently underway at the CEE (Civil and Environmental Engineering)...

The bridge, is now open for public use and is expected to serve thousands of people daily. This achievement is...

The Ethio-China Drivers Training School is pleased to announce the start of registration for new students. Aspiring drivers are invited...

FDRE technical and vocational training institute Technobizia has started working with the motto "we train as we produce, we train...

In a significant move towards enhancing infrastructure and improving connectivity in the region, Technobizia, HELVETAS, and the Oromia Construction Bureau...

Technobizia